የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መደበኛ ስብሰባ አካሄደ
ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም
የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በትላንትና ዕለት ባደረገው ስብሰባ ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከው የተልዕኮ ትግበራ ማኑዋል መነሻነት የተዘጋጀው የዩኒቨርስቲው የተልዕኮ ልየታ የትግበራ ስትራቴጂ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በዚሁ ወቅት የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ እንደተናገሩት ለዩኒቨርስቲ በተሰጠው የተልዕኮ ልየታ መሰክ መሰረት ተደርጎ ረጅም ግዜ ተሰጥቶ ሰነዱ የተሰራ መሆኑን በመግለፅ የትግበራ ስትራተጂው ዩኒቨርስቲው የሪፎርም አጀንዳዎችን ከመተግበር ኣካያ ወደፊት ለመውሰድ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል። በቀረበው ረቂቅ ሰነድም የተለያዩ ሀሳብና አስተያዬቶች በሰኔት አባላቶች ተሰጥተውበታል። በተጨማሪም የዩኒቨርስቲው ሰኔት የ2018 ዓ.ም አካዳሚክ ካላንደር ተወያይቶ አፅድቀዋል።