በሰላም ዕድሎችና አማራጮች ላይ ያተኮረ የሰላም ሰሚናር እየተካሄደ ነው።

 በሰላም ዕድሎችና አማራጮች ላይ ያተኮረ የሰላም ሰሚናር እየተካሄደ ነው።

በሰላም ዕድሎችና አማራጮች
ዛሬ ሰኔ 22/2016 ዓ/ም መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሕ/ሰብ ቋንቋዎች ኮሌጅ፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና የትግራይ ትምህርት ቢሮ በመተባበር "የሰላም ግንባታ ተግባቦት በጦርነት ባለፉ ማሕበረሰቦች ዕንቅፋቶች፣ አማራጮች፣ ዕድሎችና የባለድርሻዎች ሚና" በሚል ከትግራይ፣ አማራና ዓፋር ክልሎች የመጡ የሚሳተፉበት ሰላም ላይ ያተኮረ ሰሚናር በትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል:: በሰሚናሩ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማሕበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዚደንት ደ/ር እያሱ ያዘው ዕንቅፋቶችን ወደ ተስፋ፤ አማራጮችን ወደ ዕድል፤ ዕድሎችን ወደ ዘላቂ ሰላም ለመቀየር ባለድርሻ አካላት ያላቸው ሚና የላቀ መሆኑን አስምረውበታል።

በሰላም ዕድሎችና አማራጮች1
የሕ/ሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ ዲን ደ/ር ተስፋ ኣለም ገ/ዮሃንስ በበኩላቸው “ሰላም ከእኛ በላይ ሊያጣጥማት የሚችል ማሕበረ ሰብ የለም!“ በማለት ሰላም በጦርነት ላለፉት ማሕበረሰቦች ያላትን አስፈላጊነት አበክረው አስምረውበታል ::