መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ እና ጩራ አቦጊዳ የኪነጥበብ ማእከል ጋር በመተባበር ለሶስት ቀናት የሚቆይ ወጣቶችና የሰላም ግምባታ ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነዉ።
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምትኩ ሃይለ አዳራሽ እየተካሄደ ባለዉ ኮንፈረስ ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ የሚኖራቸዉ ሚና፣ ተሳትፎ፣ ዉክልናና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የምርምር ስራዎች ቀርበዋል።
በኮንፈረንሱ ከ 500 በላይ ከትግራይ ኣብዛኛዎቹ ወረዳዎች የተወከሉ ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።