ለልዩ የክረምት የትምህርት አመራር አሰልጣኞች በሙሉ፦
መቐለ ዩኒቨርስቲ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ከ 23/2016 እስከ ነሐሴ 15/2016 ዓ/ም የሚቆይ ከትግራይ ክልል ለተውጣጡ የትምህርት አመራር አካላት ስልጠና ለመስጠት የሚያስችለው በቂ ዝግጅት ማድረጉ ይታወቃል።
በዚህ መሠረትም ሰልጣኞች ወደ መቐለ ዩኒቨርሰቲ ዋናዉ ግቢ የሚገቡበት ቀን ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ/ም እስከ ቀኑ 6:00 ድረስ መሆኑን ያስታውቃል።
ሰልጣኞች ወደ ዋና ግቢ ሲመጡ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስና ለስልጠናው ጠቃሚ የሆኑ መጽሐፍት፤ እንዲሁም ከተቻለ Smart Phone ይዘው እንዲመጡ እናሳስባለን።
መቐለ ዩኒቨርስቲ