በአገርአቀፍ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያው ዙር ኦሬንቴሽን በመሰጠት ላይ ነው።

 በአገርአቀፍ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያው ዙር ኦሬንቴሽን በመሰጠት ላይ ነው።
ዘንድሮ በአገርአቀፍ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በአንደኛ ዙር ለሚፈተኑት 11,362 ተማሪዎች ዛሬ ሰኞ ሐምሌ1/2016 ኦሬንቴሽን እየተሰጠ ይገኛል። እነዚህ የአንደኛ ዙር ተፈታኞች ከነገ ማክሰኞ ሐምሌ 2/2016 ዓም ጀምሮ ለፈተና የሚቀመጡ ይሆናል።
እንዲሁም በሁለተኛ ዙር የሚፈተኑት 8404 ተማሪዎች የሚቀጥለው ሰኞ ኦሬንቴሽን ተሰጥቶአቸው ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ጀምሮ ለፈተና እንደሚቀመጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክስ ፕሮግራም ዳይሬክተር እና የመርኃ ግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ጎይትኦም ገብረዮሃንስ አስታውቀዋል።
በሁለቱም ዙር በዋና ግቢ፣ በዓዲ ሓቂ እና በ ቃላሚኖ ካምፓሶች በሚገኙ 6 የመፈተኛ ጣብያዎች በጠቅላላ 19,766 ተፈታኞች ለፈተና የሚቀመጡ ሲሆን፤ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ከ500 በላይ ፈታኞች እንደሚሳተፉም ዶ/ር ጎይትኦም ጨምረው ገልፀዋል።
ማሳሰቢያ:-
ነገ ማክሰኞ የሚጀመረውን ፈተና ከነገወድያ እንደሆነ እየተወራ እንዳለ መረጃ ደርሶናል። ሆኖም ይህ ከእውነት የራቀ አልቧልታ በመሆኑ፤ የአንደኛ ዙር ፈተና ነገ እንደሚጀምር በጥብቅ እናሳውቃለን።