ጥብቅ ማስታወቂያ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ
ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።
ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ እየቀረበ ያለው መረጃ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ መሆኑን እየገለጽን ፈተናው በሁለቱም በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ በድጋሜ እንገልጻለን።
በመሆኑም ተማሪዎች ይሄንኑ ተገንዝባችሁ ዝግጅታችሁን እንድትቀጥሉ ሆኖ ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ እንደተለመደው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑንና ለዚህም ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጉን እናስገነዝባለን።
ትምህርት ሚኒስቴር