አዲስ ለገቡ የክረምት ትምህርት ሰልጣኝ መምህራን የኢ-ለርኒንግ (e-Learning) ኦሬንቴሽን ተሰጠ

 ​መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ትምህርት ሰልጣኝ መምህራን ትምህርታቸውን በኦንላይን እንዴት መከታተል እንደሚችሉ የሚያስገነዝብ የኢ-ለርኒንግ (e-Learning) ገለፃ ሰጠ።

e Learning2018
​የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የኢ-ለርኒንግ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መስፍን እዮብ እንደገለጹት፤ ዓለም ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እየተሸጋገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሮኒክስ አማራጮችን በመጠቀም የሚካሄደው የመማር-ማስተማር ሂደት አሳታፊ፣ ተደራሽ እና ከተቀረው ዓለም ጋር ተወዳዳሪ የሚያደርግ ነው።
​በገለፃው ወቅት ሰልጣኞች በዋናነት፦
​የኢሼ (e-SHE) ፕላትፎርም አጠቃቀም፦ የሶፍት ስኪልስ (SS) ኮርሶችን በኦንላይን በመውሰድ ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድ፣
​የተቋማዊ ኢ-ሜይል አጠቃቀም፦ ኦፊሴላዊ የመረጃ ልውውጥና የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች አጠቃቀምን፣
​የተለዋዋጭ ትምህርት እድል፦ ከገፅ ለገፅ ትምህርት በተጨማሪ በየትኛውም ቦታ ሆነው ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት፣ አሳይመንቶችን በቀላሉ የሚሰሩበትና ፈጣን ግብረመልስ የሚያገኙበትን ሁኔታ ከተግባር ጋር የተሳሰረ ግንዛቤ አግኝተዋል።
​በዛሬው ዕለት በተካሄደው በዚህ የኦንላይን ትምህርት ገለፃ ላይ 600 ገደማ የሚሆኑ የክረምት ትምህርት ሰልጣኝ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።
e Learning2018
e Learning2018

Related Articles