
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና በወረቀት (Paper-based) የሚወስዱ ተማሪዎች ፈተናቸውን ዛሬ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በይፋ መውሰድ ጀምረዋል።
ፈተናውን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፋና ሓጎስ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ፣ እና የመቐለ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃይላይ አረጋዊ በጋራ በመሆን በይፋ አስጀምረውታል።
ፈተናው በዩኒቨርሲቲው በሁለቱ ግቢዎች — በዋናው ግቢ እና በዓዲ ሓቂ ግቢ — የሚሰጥ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኞች አስፈላጊውን ዝግጅት እና ሙሉ መስተንግዶ በማጠናቀቅ ተማሪዎችን ተቀብሏል ዛሬ በይፋ ተጀምረዋል።
ከዛሬ ሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ ፈተና በአጠቃላይ 7,774 ተማሪዎች የሚፈተኑ ይሆናል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ መልካም እድልና ስኬት እንመኛለን!
