እንኳን ደስ አላችሁ

 እንኳን ደስ አላችሁ! 
​የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ ተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል! 
​ትናንት ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በተመራቂ ተማሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየውና ውጤታማ የነበረው የልምድ ልውውጥ መድረክ ዛሬ ወደ ዋናው የምረቃ በዓል ተሸጋግሯል። 

 እንኳን ደስ አላችሁ 1
​ይህ በተለይ ለዓለም አቀፍ ተማሪዎቻችን የተዘጋጀ ልዩ የምረቃ መርሃ-ግብር (2nd International Students' Commencement Ceremony) በአሁኑ ሰዓት በደማቅ ሁኔታ እየተገባደደ ይገኛል። በአሁኑ ወቅትም ለተመራቂ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት እየተሰጠ ይገኛል! 
​ይህ ታላቅ ስኬት ለዩኒቨርሲቲያችንም ሆነ ለተመራቂ ተማሪዎቻችን ኩራትና የላቀ ውጤት ነው። ለተመራቂዎቻችን በሙሉ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን! 
#MekelleUniversity #Graduation2026 #InternationalStudents #CommencementCeremony #EducationForChange #Ethiopia #Mekelle

Related Articles