ሕዳር ፅዮን ስፖርታዊ2017

ሕዳር ፅዮን ምክንያት በማድረግ በኣክሱም ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ሕዳር ፅዮን ካፕ ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ ።
በዚህ የወዳጅነት ስፖርታዊ ውድድር መቐለ ዩኒቨርሲቲ ፣እክሱም ዩኒቨርሲቲ ፣ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ና ራያ ዩኒቨርሲቲ በ እግር ኳስና በ መረብ ኳስ ተሳትፈዋል ።
በዚህ ውድድር መቐለ ዩኒቨርሲቲ በ መረብ ኳስ ዓዲ ግራት ዩኒቨርሲቲን በማሸነፍ የ ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን በእግር ኳስም ሁለተኛ ደርጃ በመያዝ ውድድሩን ኣጠናቀዋል ።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልኡካን ቡድን ይህ ውድድር መዘጋጀቱ በዩኒቨርሲቲዎቹ መካከል ትልቅ ወዳጅነት የሚፈጥር በመሆኑ በቀጣይም ትኩረት ተሰጥቶት ቢሰራ መልካም እንደሆነ ገልፀዋል።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የ መረብ ኳስ ተጫዋች መምህር ሃይለ በርሀ የዘንድሮ የመረብ ኳስ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ በመመረጥ ተሸላሚ ሆኗል።