የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የበጎ ፈቃድ  ተሳታፊ ተማሪዎች አቀባበል ተደረገላቸው።

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የበጎ ፈቃድ ተሳታፊ ተማሪዎች አቀባበል ተደረገላቸው። ዘንድሮ በ ሃገር ደረጃ ለሚካሄደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ኣገልግሎት ተሳታፊ የሆኑ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቃላሚኖ ግቢ የአቀባበል ስነሰርዓት ተደረግላቸው ። በዚህ የበጎ ፈቃድ ተሳታፊ 109 ሴቶች፣ 356 ወንዶች በአጠቃላይ 465 የሚሆኑት የመጀመርያ አመት ተማሪዎች ሲሆኑ የማህበረሰብ ኣገልግሎት በሚሰጡበት መቐለ ዛሬ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። እነዚህ ተማሪዎች ከከተማው አስተዳደር ጋር በመተባበር ማህበረስቡን በሚያስፈልጉት ቦታዎች ሁሉ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በመስራት ለሚቀትጥሉት 25 ቀናት ቆይታ የሚያደርጉ ይሆናል።

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የበጎ አቀባበል 1