በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መስፍን ነገዎ የተመራ ቡድን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አካሂደዋል።

 በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መስፍን ነገዎ የተመራ ቡድን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አካሂደዋል።
በፕሬዚዳንት ፋና ሓጎስ የሚመራው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ከልዑካን ቡድኑ፣ ከፕሮጀክቱ ኮንትራክተሮችና ከፕሮጀክቱ አማካሪዎች ጋር ከጦርነቱ በኃላ ፕሮጀክቶቹ ስላሉባቸው ደረጃዎችና፤ ለመቀጠል ስላሉባቸው ተግዳሮቶች በሰፊው ተወያይተዋል። በተጨማሪም ባለድርሻዎቹ ፕሮጀክቶቹን ለመቀጠል የሚያስችሉ መፍትሔዎች በተመለከተ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በመጨረሻም ከኮንስትራክሽን ባለስልጣኑ በተሰጠ አቅጣጫ መሠረት ከባለስልጣኑ፣ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ራያ ዩኒቨርሲቲና አክሱም ዩኒቨርስቲ የተውጣጡ የኮንስትራክሽንና ዲዛይን ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ኮንትራክተሮቹና አማካሪዎቹ የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት አካሂዶ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲያስቀምጥ ተስማምተዋል።
የሚቋቋመው ኮሚቴ ስራዎች የተሳኩ እንዲሆኑ ባለድርሻዎቹ በሙሉ ተነሳሽነት እንደሚሰሩ በመዝግያ ስነ ስርዓቱ ላይ አሳውቀዋል።

 ኢኮ ኢንጅነር መስፍን ቡድን መዩ1