በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ ወጪ የተገነባው የ ቅዱስ ያሬድ መታሰብያ ሃወልት ዛሬ በአክሱም ከተማ በይፋ ተመረቀ።

 በመቐለዩኒቨርሲቲ የ ቅዱስ ያሬድ  

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ ወጪ የተገነባው የ ቅዱስ ያሬድ መታሰብያ ሃወልት ዛሬ በአክሱም ከተማ በይፋ ተመረቀ።
በግንቦት 2011 ግንባታው የተጀመረው ይህ ሃውልት በ ኮሮናና ቀጥሎም በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ተስተጓጉሎ ቆይቶ ከአምስት አመታት በኋላ የተጠናቀቀ ሲሆን ብፁእ አብነ መርቃርዮስ የማእከላዊ ትግራይ አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን ኣባቶች፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ፣የትግራይ ቱሪዝም እና ባህል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አፅበሃ ገብረዝጋብሄር አና ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች እና የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተመርቋል።

 በመቐለዩኒቨርሲቲ የ ቅዱስ ያሬድ1