በመቐለ ዩኒቨርስቲ ሲካሄድ የቆየው የዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንቶች ፎረም ተጠናቀቀ ።

በመቐለ ዩኒቨርስቲ ሲካሄድ የቆየው የዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንቶች ፎረም ተጠናቀቀ ።
ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ የትምህርት ጥራት ጉዳዮችና የማሻሻያ አማራጮችን በተመለከተ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው በኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፕረዚደንቶች ፎረም ዛሬ አመሻሽ ተጠናቀቀ ።


በሁለት ቀን የውይይት ፕሮግራሙም ከተሳታፊዎች በርካታ አንገብጋቢ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ታሳቢ ቢደረጉ ያሏቸው ነጥቦችም አክለዋል ።
ተሳታፊዎቹም በትምህርቱ ዘርፍ በተደጋጋሚ ይስተዋላሉ ያሉዋቸውን ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱም ጠይቀዋል ።


የሙያ ማእከላት ለማጠናከር የሚያግዙ ፖሊሲ አማራጮች በተመለከተም ከተሳታፊዎቹ ምሁራዊ እይታዎች ቀርበዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ በቂ አይደሉም ባሉዋቸው ጉዳዮች አስተያየት በመስጠት ውይይቱ በቀጣይም በሌላ ዙር የምክክር መድረኮች እንዲቀጥል ተሳታፊዎች ጠይቀዋል።
በተነሱት ጉዳዮች ላይ አስተያየት የሰጡት የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ስመኝ ዉቤ በቀጣይ አስፈላጊ ያሉትን ክትትልና ሪፖርት በየጊዜው በማድረግ የስራውን ስኬት ግምገማ ሂደት እንደሚደረግ ጠቁመዋል ።


በትምህርት ሚኒስትር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ኢባ ምጀና በበኩላቸው የመውጫ ፈተና ፥የክረምት ትምህርት ዝርዝር መላክ በቂ ዝግጅት እንዲደረግ መልእክት አስተላልፈዋል ።


በኢፊድሪ የትምህርት ሚኒስትር ሚንስትር ዲኤታ ኩራ ጡሹኔ በመዝግያ ንግግራቸው ፎረሙ ተዘጋጅቶ በመልካም ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የ መቐለ ዩኒቨርስቲና አመራሮች አመስግነዋል ።


የተነሱ ሃሳቦች ወደ መሬት ለማውረድ ከሁሉም አካላት ቁርጠኝንነት ይሻል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በተለያዩ ጉዳዮች በቀጣይ ተከታታይ ስልጠናዎችም ይሰጣሉ ብለዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ የተነሱ ብዙ ችግሮች እንዲፈቱም ጥረት እየተደረጉ ነው ሲሉ አክለዋል።
እንደ ሚኒስትሩ እምነት በዘንድሮ የበጀት አመት ተሻለ የጥገና በጀት ይኖራል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ገልፀዋል።