የ2016 ዓም በአገርአቀፍ የሚካሄደው የ12ኛ ክፍል የአንደኛው ዙር መልቀቅያ ፈተና መርኃ ግብር በስኬት መጠናቀቅ አስመልክቶ የምሳ እና የምስጋና ዘግጅት ተደረገ።

 የ2016 ዓም በአገርአቀፍ የሚካሄደው የ12ኛ ክፍል የአንደኛው ዙር መልቀቅያ ፈተና መርኃ ግብር በስኬት መጠናቀቅ አስመልክቶ የምሳ እና የምስጋና ዘግጅት ተደረገ።

ዛሬ እሁድ ሐምሌ 07/2016 ዓም የ2016 ዓም በአገርአቀፍ የሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና መጀመርያው ዙር በስኬት መጠናቀቁ ምክንያት በማድረግ ለፈተናው መሳካት ፈታኞች፣ የፈተና አስተባባሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ አባሎች፣ የትግራይ ክልል ፖሊስ አባሎች፣ የትምህርት ቢሮ አስተባባሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለነበራቸው ጉልህ ሚና የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸዋል።
በፕሮግራሙ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ንግግር ያደረጉት የአስተዳደር ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ተኸስተ ብርሃኑ ይህ በታላቁ ዕለተ ሰንበት የተካሄደው የምስጋና ዝግጅት በአንደኛ ዙር የነበረው ስኬት በሁለተኛው ዙር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስታወስና፤ ለፈተናው ከመጡት እንግዶች ጋር ቤተሰባዊ የዕረፍት ቀን ለማሳለፍ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
የዕለቱ የምስጋና ሕብሽቲ/አምባሻ/ በዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ዶ/ር ፋና ሐጎስ፣ በትግራይ ክልላዊ መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር የማሕበራዊ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክረታርያት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፤ እንዲሁም በፌደራል ፖሊስ የሰሜን መምርያ አዛዥ ኮማንደር ዝናቡ ኃይሌ ተቆርሷል።