Featured

የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

 የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ
ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ የሚካሄደው ከሐምሌ 24 - ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ስለአመዘጋገቡ ሂደት ጋይዱን በደንብ ያንብቡት።
@gizachew_ki

ለልዩ የክረምት የትምህርት አመራር አሰልጣኞች በሙሉ፦

መቐለ ዩኒቨርስቲ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ከ 23/2016 እስከ ነሐሴ 15/2016 ዓ/ም የሚቆይ ከትግራይ ክልል ለተውጣጡ የትምህርት አመራር አካላት ስልጠና ለመስጠት የሚያስችለው በቂ ዝግጅት ማድረጉ ይታወቃል።
በዚህ መሠረትም ሰልጣኞች ወደ መቐለ ዩኒቨርሰቲ ዋናዉ ግቢ የሚገቡበት ቀን ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ/ም እስከ ቀኑ 6:00 ድረስ መሆኑን ያስታውቃል።
ሰልጣኞች ወደ ዋና ግቢ ሲመጡ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስና ለስልጠናው ጠቃሚ የሆኑ መጽሐፍት፤ እንዲሁም ከተቻለ Smart Phone ይዘው እንዲመጡ እናሳስባለን።
መቐለ ዩኒቨርስቲ

ጥብቅ ማስታወቂያ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ (2)

 

 ጥብቅ ማስታወቂያ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።
ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ እየቀረበ ያለው መረጃ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ መሆኑን እየገለጽን ፈተናው በሁለቱም በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ በድጋሜ እንገልጻለን።
በመሆኑም ተማሪዎች ይሄንኑ ተገንዝባችሁ ዝግጅታችሁን እንድትቀጥሉ ሆኖ ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ እንደተለመደው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑንና ለዚህም ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጉን እናስገነዝባለን።
ትምህርት ሚኒስቴር