ኦሪጅናል ዲግሪ ሰርተፊኬት ላልወሰዳችሁ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂዎች በሙሉ

ኦሪጅናል ዲግሪ ሰርተፊኬት ላልወሰዳችሁ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂዎች በሙሉ
​ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተመርቃችሁ ዋናውን ኦሪጅናል ዲግሪ (Original Degree) ሰርተፊኬት ላልወሰዳችሁ እና እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉ የዩኒቨርሲቲያችን የቀድሞ ተመራቂዎች ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የኦሪጅናል ዲግሪ የህትመት መመሪያ መሰረት ለማሳተም የዝግጅት ስራዎች ጀምረናል። ስለዚህ ሁላችሁም አመልካቾች በGoogle form link https://forms.gle/vbNH5Z5uBd5HFho77 በመጠቀም ትክክለኛ መረጃ በመሙላት እስከ ግንቦት 26, 2018 ዓ.ም ድረስ የማመልከቻ ቅጹን እንድትሞሉ እናሳስባለን።
​ማሳሰቢያ፦
​በወጪ መጋራት (Cost-Sharing) የተማራችሁ አመልካቾች ኦሪጅናል ዲግሪ ሰርተፊኬታችሁን ለመውሰድ የክፍያ ግዴታችሁን መፈጸማችሁን ወይም በአገልግሎት መወጣታችሁን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እና ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
ኦሪጅናል ዲግሪ ሰርተፊኬት ላልወሰዳችሁ

Related Articles