የዓድዋ ድል ተደራጅቶ

የዓድዋ ድል ተደራጅቶ በመታገል ከባርነት መውጣትና ነፃነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ለዓለም ያስተማረ ተሞክሮ ነው — የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን

የዓድዋ ድል ተደራጅቶ

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ፣ የባህል ጥናትና ምርምር ክፍል ምሁራንና ተመራማሪዎች፣ 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ "የዓድዋ ድል በታሪክ፣ በሥነ-ጽሑፍና በሚዲያ እይታ" በሚል ርዕስ የምርምር ጽሑፎችን በማቅረብ ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶክተር ዝበሎ ተስፋማርያም በይፋ ከፍተውታል።

የዓድዋ ድል ተደራጅቶ
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁራንና ተመራማሪዎች የሆኑት ዶክተር ገብረየሱስ ተክሉ እና ዶክተር ሙሉብርሃን አዳነ፤ የዓድዋ ድል ተደራጅቶ በመታገል ከባርነት መውጣትና ነፃነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ለዓለም ትልቅ ተሞክሮ ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ጽሑፍ መምህርና የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት አቶ እንዳሻው ሎቲራ ዋግጅራ፣ የዓድዋ ድል በሚዲያ ስለሚሸፈንበት ሁኔታ ባቀረቡት ጽሑፍ፤ የፖለቲካ መሪዎች ለፖለቲካዊ ጥቅማቸው ሲሉ የበዓሉን ድምቀት የሚያደበዝዙና ተገቢውን የታሪክ እሴት እንዳያገኝ የሚያደርጉትን ስሕተት ሊያርሙ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ምሁራኑ እንደገለጹት፤ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ እና የፓን-አፍሪካኒዝም መሠረት የጣለው የዓድዋ ድል፣ ታሪኩ ሳይዛባ ተጠብቆና ተሰንዶ ለቀጣዩ ትውልድ ሊተላለፍ ይገባዋል።
ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበብ እና የኢትዮጵያውያን አንድነት የታየበት የዓድዋ ድል፣ የቱሪዝም ምንጭ ሆኖ ለሀገር ጥቅም እንዲውል ሕዝብና መንግሥት ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባም ምሁራኑ አስገንዝበዋል።

የዓድዋ ድል ተደራጅቶ
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የባህል ጥናት ክፍል ኃላፊ አቶ ኪሮስ ገብረዮሐንስ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የዓድዋ ድል እሴቶች ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉና ለሀገር ጥቅም እንዲውሉ ምርምርና ጥናት በማድረግ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

Related Articles