ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
በ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በግል ከፍለው ወይም በተቋማቸው ስፖንሰርነት መማር ለሚፈልጉ የመጀመሪያ ዲግሪ (በማታ) ፣ የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የትምህርት መስኮች ዝርዝርና መርሃ ግብር ከ https://www.mu.edu.et/images/MU_Academic_Programs2018EC.pdf መረጃ ማግኘት የሚቻል ሲሆን አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ድህረ፟-ገጽ https://portal.mu.edu.et/ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፣
የትምህርት ማስረጃ ፤
የNational Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት (ለ 2ኛና 3ኛ ዲግሪ አመልካቾች) ፣
የትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት ያሟሉ የ 1ኛ ዲግሪ የማታ አመልካቾች፣
ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ (Application processing fee 200 ብር(ለ 1ኛና 2ኛ ዲግሪ) እንዲሁም 300 ብር(ለ3ኛ ዲግሪ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ MU-ICDE ስም ሂሳብ ቁጥር 1000015320207 ገቢ ማድረግ
ከላይ የተጠቀሱት ሰነዶቸ/ማስረጃዎች ስካን ተደርጎ በማመልከቻ ድህረ-ገጹ ላይ መጫን ይኖርባቸዋል።
መቐለ ዩኒቨርሲቲ