የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሕዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎች ፎረም እየተካሄደ ነው
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ከመጋቢት 27-28/ 2017 ዓ/ም የሚካሄደው የመንግሥት ዩኒቨሲቲዎች የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎች ፎረም መካሄድ ጀምሯል።
ፎረሙ የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ስልቶችና እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሚዩኒኬሽን ተግባራት ልምድ የሚቀርብበት፣ ዓመታዊ ዕቅዶችና የአፈጻጸም ሪፖርቶች የሚገመገሙበት ብሎም በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ የሚሰጥበት መድረክ ሲሆን የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መሠረታዊ ሐሳቦች እና ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት መስክ ወሳኝ አጀንዳዎችን አስመልክቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ ግንዛቤ የሚጨብጥበት እንዲሁም ዘርፉን አስመልክቶ ከተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ የሚቀሰምበት
ነው፡፡
በመድረኩ የሕዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳምሶን መኮንን ፣ በት/ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ፣ በት/ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ቦጋለ፣ የአረባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ ፕሬዝደንትና የፕሬዝደንት ተወካይ ዶ/ር ኢ/ር ቦጋለ ገ/ማርያም እና ሌሎች ዩዩኒቨርሲቲው አመራሮች ተገኝተዋል።